=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
ሂጃብ አንዲትን ሴት በኢስላም ያላትን ደረጃ እንድትረዳ የሚያደርግ መሆኑ ጥርጥር የለውም። ሂጃብሽን መልበስሽ ሃያእ(ይሉኝታ) እንዲኖርሽ እና እንድታዳብሪው ያደርግሻል። ይህን በማድረግሽ አሏህ የተሻለን ነገር ያጐናፅፍሻል።
ሂጃብ ራስን ከመጥፎ ነገር መከለያ ነው።
መልእክተኛው(ሰ.ዐ.ወ) ከባሏ ቤት ውጭ ሆና እራሷን የገላለጠች ከሏህ የተሰጣት የሆነን መከለያዋን ጥሳለች ብለዋል። {አህመድ አልባኒ ሰሂህ ብለውታል}
ሂጃቧን ያደረገች ሴት በዚህ አለምም ሆነ በመጭው አለም ከጌታዋ አሏህ የሆነን መከለያ ታገኛለች፤ ከጀነት ነዋሪዋችም መካከል ትሆናለች።
ሂጃብ የፊጥራ ክፍል ነው።
ሂጃብ የፊጥራ (የተፈጥሮ ባህሪ) ክፍል ነው። ይህን በጥልቅ ለመረዳት ተፈኩር (ማስተንተን) ጠቀሚ ነው። በዙሪያሽ ያሉ ነገሮችን ተመልከች ሁሉም ሽፋን አላቸው:: ለምሳሌ መሬት በከባቢ አየር የተሸፈነች ናት፤ የውስጥ የአካል ክፍሎች፣ ሴሎች ፣ ማእድናት ፣ ፍራፍሬ ወዘተ የራሳቸው የሆነ መሸፈኛ አላቸው፤ ቆዳሽ ብርሃን አስተላላፊ ቢሆን ኖሮ ምን ልትመስሊ እንደምትችይ አስቢው:: ባጠቃላይ መሸፋፈን መከናነብ የስነ-ፍጥረት ህግ ነው ማለት ይቻላል። አሏህ እራስሽን እንድትሸፋፍኝ ደንግጐታል።....Read more
የምእራቡ ቁሳዊ ሂወት የመንፈስ መበላሸትን ያበረታታል። ማህበራዊ ትስስር ወይም ዝምድና የሚባለው ነገር ንትርክ የበዛበት ፣ ግለኝነት እና ከመተባበር ይልቅ ውድድር የሚስተዋልበት ነው። ይህ መገለጫ ባህሪ ኢስላም ከሚያበረታታው መንፈሳዊ ሂወት በተቃራኒ ነው። ኢስላም አማኞቹን ጤናማ የሆነ ማህበራዊ ኑሮን እንዲመሰርቱ ፣ ለሰወችም ቅርብ እንዲሆኑ ፣ ዝምድናን እንዲቀጥሉ እና ከግለኝነት ይልቅ ትብብር የተሞላበት ሂወትን እንዲመሩ ያዛል።
አንድ ሙስሊም ሴት እህቶቿን እንዴት ነው የምትንከባከባቸው?
1) ለአሏህ ብላ ትወዳቸዋለች
ይህ ፍቅር በማንኛውም አለማዊ አና ስውር ጥቅም ያልተመረዘ የሆነ ነው። እውነተኛ የእህትነት ፍቅር ከኢስላም መመሪያ ብርሃን የሚመነጭ ግኑኝነት ወይም ማህበሪዊ ትስስር ነው። እንዲሁም አንዲት ሙስሊም ሴትን ጁኦግሪፊያዊ መነሻ ፣ ጐሳ ፣ የቆዳ ቀለም ፣ የአይን ቀለም ወይም የፀጉር ቴክስቸር እና ቇንቇ ሳይገድባት ከእህቶቿ ጋር ልብ ለ ልብ የሚያስተሳስር ብቸኛ ሰንሰለት ነው። ሰንሰንሰለቱም መሰረት ያደረገው የአሏህን(ሱ.ወ.ተ) እምነት ነው።....Read more
ሂጃብና ኒቃብ እንዲሁም ቡርቃ የብዙ አለመግባባትና የክርክር አርዕስቶች ከሆኑ ብዙ ዘመናትን አሳልፈዋል። ብዙ ሃገሮች እነዚህን ሃይማኖታዊ አልባሳት የከለከሉ ሲሆን አንዳንድ ሃገሮች ደግሞ የት የት ቦታ መለበስ እንዳለባቸው ገደብ አስቀምጠዋል።
በኒቃብ እና በቡርቃ ላይ ብዙ ክርክሮች የተደረጉ ሲሆን ኒቃብ ጭቆናና ኋላቀርነት ነው የሚሉ ትችቶችም ከተለያዩ ሰዎች ይሰነዘራል። እናም ዛሬ የምናየው እውነት ኒቃብ እና ቡርቃ የኋላቀርነት እና የጭቆና መገለጫዎች ናቸውን? የሚለውን ነው።....Read more
አንደኛዉና ዋነኛዉ አማኝ ሴትን ልዪ የሚያደርጋት ባህሪያቶች በአላህ ያላት እምነት፤ የፀና እምነቷ በዚህ አለም የተከሰተዉ ቢከሰት መጥፍ አጋጣሚወች ቢፈጠሩ በአላህ ፍቃድ ነዉ የምትል የሆነች ናት::
የትክክለኛ ሙስሊም ሴት እምነቷ ወይም አቂዳዋ ንፁህ እና ግልፅ ሲሆን በድንቁርና እድፍ ፣ በተሳሳተ አመለካከት እና ጥንቆላ ያልተበከለ ወይም ያልተመረዘ የሆነ ነዉ:: እምነቷ ያአላህን እምነት መሠረት ያደረገ ፣ አንድነቱን ፣ ከሁሉ በላይ መሆኑን ፣ ዘላለማዊነቱን ፣ ሁሉን ማድረግ የሚችል መሆኑን ፣ ሙሉ አለምን ተቆጣጣሪ እና ሁሉም ነገር ወደርሱ ተመላሾች መሆናቸውን በማመን....Read more
በቀላሉ ባለባበሴ ምክኒያት እኔን ተመልክታችሁ ጭቁን ስትሉ ትጠሩኛላችሁ።
ከውስጤ ያለውን ሳታውቁ በኩራት የለበስኩትን ልብስ ትገመግማላችሁ....Read more
እውነተኛ የእህትነት ፍቅር ከኢስላም የመመሪያ ብርሃን የሚመነጭ ግኑኝነት ወይም ማህበሪዊ ትስስር ሲሆን ይህ ፍቅር በማንኛውም አለማዊ አና ስውር በሆነ ጥቅም ያልተመረዘ ነው። አንዲትን ሙስሊም ሴት ጁኦግሪፊያዊ መነሻ ፣ ጐሳ ፣ የቆዳ ቀለም ፣ የአይን ቀለም ወይም የፀጉር ቴክስቸር እና ቇንቇ ሳይገድባት ከእህቶቿ ጋር ልብ ለ ልብ የሚያስተሳስር ብቸኛ ሰንሰለት ነው። ሰንሰለቱም መሰረት ያደረገው የአሏህን(ሱ.ወ.ተ) እምነት ነው።....Read more
ንትርክ ወደ በለጠ አለመግባባት እና ድርቅና ያመራል፤ ለኢብሊስም ክፍት ቦታ ይፈጥራል። አብዛሃኛውን ጊዜ ስሜትን የሚጐዳ የሆነ ቀልድ ጥላቻ እና ክብር ማጣትን ያስከትላል። ቃልኪዳንን ማፍረስ ሰዎችን ሲያበሳጭ በመካከላቸው የነበረውንም ፍቅር ጥላሸት ይቀባዋል። የሚያቆራርጥን ነገር ላለመናገር ማፈግፈግን መማር ይኖርብናል። አንዳንዴም ችግሩ የተሻለ እውቀት ባለው ሰው እስኪፈታ ድረስ "ላለመስማማት መስማማት" ይኖርብናል።....Read more
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|